ዜና ቤተክርስቲያን መጻሕፍት ጠቃሚ
ቤተማርያም Btemariam
የሶሻል መረቦች መዝሙሮች ሊያሳስበን የሚገባ ከሚታዩ
Betemariam.org :-ይህ መካነ ድር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የቀን መቁጠሪያ ከንግጻዌው የያዘ ነው

 

        

      ግጻዌ       
መስከረም ጥቅምት ኅዳር ታኅሣሥ  ጥር የካቲት 
መጋቢት ሚያዝያ ግንቦት ሰኔ ሐምሌ ነሐሴ

ጳጉሜን  በተውሳክለሚወጡናለሚር ዘዐቢይ ጾም

 
 
ማህተብህን በጥስ ???? ገመድ የምትበላ ብትሄድ ጠፍር የምትበላ ትመጣለች በኢሕአዴግ የአዲስ አበባ አደረጃጀቶች ስለ አክራሪነት በተካሔደ ውይይት በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የተሰነዘረው ፍረጃና ክሥ ተሳታፊዎችን አስቆጣ የጅማ ዩኒቨርስቲ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ ተማሪዎች ለመጾም ተቸግረዋል፤ ‹‹የአምልኮ፣ የአለባበስና የአመጋገብ መመሪያ›› አፈጻጸም እንደ ሓላፊዎች እምነት የሚወሰን ኾኗል
[EOTC ] [ TTEOTV] [AKO] [ MRADIO]
ሰላም ለገጽኪ ለጥቀ ይልሂ  እምሥነ ከዋክብት ወወርኀ ወእምሥነ  ፀሐይ መብርሂ በእንተ ተሠግዎቱ ለወልደ አምላክ እምኔኪ ወብኪ ቅሩባነ ኮነ እምድር  በማኀደር ውስተ ዓርያም ብኪ ወብሰመ ወልድኪ ቅሩባነ ኮነ
አስተያየት
                                                    ሰቆቃ ወቤተክርስቲያን
                                                                     (በዲ/ ዳንኤል ክብረት)
  ክርስትናን እሳት የሚያሸንፈው ቢሆን ኖሮ ድምጥያኖስና   ዲዮቅልጥያኖስ በተሳካላቸው ነበር፡፡
  ክርስትናን መግደል የሚያሸንፈው ቢሆን ኖሮ አይሁድና ሮማውያን፣ ኮሙኒስቶችና ማኦኢስቶች ድል በነሡት ነበር፡፡
 
ክርስትና በቤተ ክርስቲያኖች መቃጠል፣ በቅዱሳት መጻሕፍትም መቆነጻጸል የሚያበቃለት ቢሆን ኖሮ ኔሮንና ትራጃን፤ ዮዲት ጉዲትና ግራኝ ባስቆሙት ነበር፡፡ ክርስትና እሳት ሆኖ በእሳት ውስጥ ማለፍ ነው፡፡
  ክርስትና እሳትን እሳት ሆኖ ድል መንሣት ነው፡፡ እዚህ እሳት ላይ ሦስቱ ሕጻናት ተጥለው ነበር፣ እዚህ እሳት ውስጥ ቂርቆስና እየሉጣ ተወርውረው ነበር፡፡ ይኼ እሳት ቅዱስ ፖሊካርፐስን በልቶት ነበር፡፡
  
ክርስትና ግን ይኼው አለ፡፡ ሊያጠፉት የተነሡት ሁሉ ተረት ሆነዋል፡፡ ክርስትና ግን ህያው ሆኖ አለ፡፡ የሠራነውን ቤተ ክርስቲያን ያቃጥሉ ይሆናል፣ የሠራነውን ሰማያዊ ቤት ግን አይደርሱበትም፡፡  ንብረታችንን ይወስዳሉ፣ እምነታችንን አያገኙትም፤ እኛን ይገድላሉ፤ ነፍሳችን ግን ከዐቅማቸው በላይ ናት፡፡
  
ይህንን መከራ አስቀድመን የማናውቀው ቢሆን ኖሮ በደነገጥን ነበር፡፡ ነገር ግን ክርስቲያን ስንሆን ይህ እንደሚመጣ እናውቅ ነበር፡፡ተዘጋጅታችሁ ተቀመጡተብለናልና ተዘጋጅተን ነበር፡፡ እኛ ቆንጨራና ቦንብ፣ መትረዪስና አዳፍኔ አንይዝም፡፡ እኛ በጠጠር ጎልያድን የሚረታውን ይዘናል፡፡ በጩኸት ሳይሆን በዝምታ ኢያሪኮን የሚንደውን ይዘናል፡፡ በሁካታ ሳይሆን በእርጋታ የሚሠራውን  ይዘናል፡፡ እነርሱ ሲጮኹ ከአጋንንት ጋር ያውካሉ፤ እኛ ግን ዝም ስንል ከፈጣሪያችን ጋር እንነጋገራልን፡፡
     ዛሬ በምድር ላይ የለኮሱትን እሳት ብዙዎች በሰማይ እነርሱው ይቀበሉታል፡፡ አይቀርም፤ አምላካችንም ዝም አይልም፡፡ እንገደላለን፤ ግን እናሸንፋለን፤ እንቃጠላለን፤ ግን እንለመልማለን፡፡ እናጣለን፤ ግን እናገኛለን፡፡ ቤተ ክርስቲያን ከተቃጠሉት ሕንጻዎቿ በላይ ናትና፡፡ የቅዱሳን አምላክ ከተዋህዶ በረት አያናውጸን፣ አምነው ነበር ካዱ፣ ተሰብስበው ነበር ተበተኑ ከመባል እመብርኃን የሁላችንንም ፍጻሜ ታሳምርልን፣ የሰማዕታቱ ምልጃና ጸሎት አይለየን።
                                                                 
ወስብኃት ለእግዚአብሔር